ወጣቶችን መሳሪያ

የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ‹‹ወጣቶችን መሳሪያ ማስታጠቅና ማደራጀት›› የሚል ክስ ቀረበባቸው . . የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ታስረው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡ አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ታስረው የሚገኙ የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ጠይቀው ሲመለሱ መሆኑን የአብን ሊቀመንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አመራሮቻቸውና አባሎቻቸው የታሰሩት በቀዝቃዛ ቦታ፣ የፀሐይ ብርሃን በማያገኙበትና ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በማይችል ሁኔታ በመሆኑ እንዲሻሻልላቸው ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተው ሲወጡ፣ መውጫ በር ላይ አቶ ክርስቲያንን እንደያዟቸው ሊቀመንበሩ … Continue reading ወጣቶችን መሳሪያ

ከዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተቶ ከዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የተሰጠ የአቋም መግለጫ —————————————— የዎላይታ ሕዝብ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት የተጎናጸፈውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ በሽግግር ወቅት በክልል ዘጠኝ ከተደራጀበት ወደ ደቡብ ክልል ተጨፍልቆ እንዲዋቀር ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ እያቀረበ የቆየ ሲሆን በተለይ በ1992 ዓ.ም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የብሔሩ ተወላጆች በጥቂት የፓለቲካ ሊህቃን የህዝቡን ማንነት የሚጨፈልቅ ሰዉ ሰራሽ “ወጋጎዳ” የተባለ ቋንቋ በሥርዓተ ትምህርት ቀርጸው በማምጣታቸዉ አደባባይ ወጥቶ ተቃዉሞ በማድረግ ህዝባዊ ትግል በማድረግ መስዋዕትነት ከፍሎ ህገ መንግስቱ እንዲከበር ፋና ወጊ ሚና በመጫወት ማንነቱን እና ህልውናውን ማስጠበቅ የቻለ እና አሁን የሚገኝበትን የዞን መዋቅር ያገኘ እና የአጎራባች ህዝቦች መብት እንዲከበር ታግሏል:: እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለአንድ … Continue reading ከዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር በአንድ ቀን መረዳት ይችላሉ

ጠቅላይ ሚኒስተራችን የተለያዩ ተቋማትን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ። ድንቅ የመሪነት ብቃት ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያን ህዝብ ብሶት ለመረዳት ሁለት ቦታ ጎብኝት ቢያደርጉ እመክራለው። አንደኛ የእናቶቻችንን ማድ ቤት እና ሁለተኛ የህዝብ ሽንት ቤት ነው። እነዚህን ተቋማት ቢጎበኙ ብቻ ሳይሆን ቢጠቀሙ እመክራለው። ይህን ማድረግ ከቻሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር በአንድ ቀን መረዳት ይችላሉ። መልካም ጉብኝት Dr.Yared Agidew Continue reading የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር በአንድ ቀን መረዳት ይችላሉ

የሚወዱትን ያላዳኑት ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ

በደርግ ዘመን የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ጊዜ 7,000(ሰባት ሺህ) አከባቢ የሚሆኑ ቤተ መፅሐፍት ተቋቁመው ነበር፡፡በጣት ከሚቆጠሩት በቀር ሁሉም ጠፍተዋል፡፡በንባብ ወዳድነቱ የሚነግርለት የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በእርሳቸው አመራር ጊዜ ቤተ መፅሐፍቱ ሲጠፉ አመራራቸው ሊያድኗቸው አልቻለም፡፡ጠቅላይ ሚኒስተሩ የሚወዱትን አላዳኑም፡፡ እነዛህ ቤተ መጽሐፍ ያለባቸው ክበቦች በዲኤስ ቲቪ የቢራ ና የድራፍት ማዕከላት ሆነው ከመፅሐፍት የተጣሉ ማዕከላት ሆነዋል፡፡ ዛሬ እያንዳዳችን ልናስብበት ይገባል Continue reading የሚወዱትን ያላዳኑት ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ

የሕክምና ባለሙያዎች ሥራ ማቆም አድማ ከሕግና ከስነ-ምግባር ያለዉ አንድምታ! ሕሊና ፈረደ እና ጤናዳም

ይህን ጦማር ለመጻፍ የተነሳነዉ ከሰሞኑን የሕክምና ባለሙያዎች ሥራ ማቆም አድማ ጋር በተገናኘ አድማዉን በመደገፍና አለመደገፍ የሃሳብ ልዩነቶች ሲንፀባረቁ በመመልከታችን ነዉ፡፡ የሕክምና ባለሙያዎች ያነሱት ጥያቄ እኛም የምንደግፈዉ ነዉ፡፡ ሆኖም ሥራ ማቆም አድማዉን በተመለከተ ከስሜታዊነትና ጀብደኝነት ወጥተን ነገሩን ከስሩ መመልከት ይሻላል በሚል ጽሁፉን አዘጋጅተናል፡፡ ጽሁፉ ከመማማርና መረጃ ከመለዋወጥ ያለፈ ዓላማ የለዉም፡፡ የማንንም ጥያቄና አጀንዳ እንዲያኳስስ ተብሎም የቀረበም አይደለም፡፡ ጽሁፉ ቢረዝምም መልካም ንባብ! ——– የስራ ማቆም አድማ! በታሪክ የመጀመሪያዉ የስራ ማቆም አድማ ሆኖ የተመዘገበዉ በ12th century BC በድሮዋ ምስር አገር (በአሁኗ ግብፅ) በንጉስ ራምሴ ሶስተኛ ዘመን መንግስት የእደ ጥበብ ባለሙያዎች ለሰሩበት ምንዳ ባለማግኘታቸዉና በነበረዉ የነቀዘ/ሙሰኛ አሰራር ምክንያት በሚደርሳባቸዉ በደል ምክንያት ያደረጉት የስራ ማቆም … Continue reading የሕክምና ባለሙያዎች ሥራ ማቆም አድማ ከሕግና ከስነ-ምግባር ያለዉ አንድምታ! ሕሊና ፈረደ እና ጤናዳም

ለጌድኦ ተፈናቃዮች የመንግስት ያለ Refugees International

Refugees International የተባለው የስደተኞች መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ ክልል በተለይም ጌዴኦ አካባቢ ተፈናቃዮችን በሀይል ወደ ቀያቸው እየመለሰ ነው ብሎ ዛሬ ከሷል። ድርጅቱ እንዳለው ይህ የመንግስት ሀይል የተሞላበት እርምጃ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ እያባባሰው ነው! Last year, in southern Ethiopia, intercommunal violence caused hundreds of thousands of people to flee their homes. Refugees International (RI) is deeply alarmed by the Ethiopian government’s renewed effort to carry out forced returns of these internally displaced people (IDPs). “The government’s actions are making an ongoing humanitarian crisis even worse,” said RI Senior Advocate Mark Yarnell, who traveled to southern Ethiopia in September 2018. “I … Continue reading ለጌድኦ ተፈናቃዮች የመንግስት ያለ Refugees International

“ልዩነታችንን አቻችለን”ዳውድ ኢብሳ

“ፓርቲዎቹ ልዩነታቸውን አቻችለው ለዚህ ውህደት መብቃታቸው እነዚህን አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ያስመሰግናቸዋል።” አቶ ዳውድ ኢብሳ በህብር ኢትዮጵያ የውህደትና የምሥረታ በዓል የተናገሩት ይህ እጅግ በተራራቀ ርዕዮት አለም ና የዘር ፓለቲካ አቋም ውስጥ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች በጋራ ሀሳብን የመካፈል ልምድ መካፈል ልምድ ለሰላማዊ ኢትዮጲያ መሰረት ነው፡፡ ውህዱን የፈፀሙት ፓርቲዎችም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት(ሽግግር)፣ ኢትዮጵያችን ህዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን)፣ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳዔ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ቱሳ)፣ የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት(ኦህዲኅ)እና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት(አረንጓዴ ኮከቦች) ናቸው። Continue reading “ልዩነታችንን አቻችለን”ዳውድ ኢብሳ