አቶ ጌታቸው አሰፋ

አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ተመሰረተባቸው ፡፡

ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪዎች ፣የማረሚያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በብሔራው መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ሲካሔድ የነበረውን የወንጀል ምርመራ ተከትሎ ነው፡፡

በዚሁ መሰረት ዓቃቤ ሕግ በወንጀል መርማሪዎች ፤ በማረሚያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ክስ ተመስርቷል፡፡

በመርማሪዎች ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከፈተው እና በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች በነበሩት ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከፈቱት መዛግብት የክስ ሂደቱ ቀጥሎ ምስክር ለመስማት ተቀጥረዋል፡፡

በሶስተኛውና በዚህኛው የመጨረሻ መዝገብ ላይ 26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በጠቅላላው 46 ክሶች ተመስርቶባቸዋል፡፡

በክሶቹ ውስጥ 22ቱ ተከሳሾች በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በሌላ በኩል የቀድሞ የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ አቶ አጽብሃ ግደይ፣ አቶ አሠፋ በላይ እና አቶ ሽሻይ ልዑል በተባሉ የቀድሞ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ በሌሉበት ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዴታ ምድብ ችሎት ክስ እንደሚመሰረትባቸው ከጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ ፡- የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s