ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዩኔስኮ የ2019 የሰላም ተሸላሚ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዩኔስኮ የ2019 የሰላም ተሸላሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት/ዩኔስኮ/ የ2019 የሰላም ተሸላሚ ሆኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሽልማት ያገኙት በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት እንዲሁም የፕረስ ነፃነት እንዲሰፍን ላደረጉት አስተዋፅኦ መሆኑ ተገልጿል።

በአፍሪካ ህብረት እየተከበረ ባለው የዓለም የፕረስ ነፃነት ቀን ላይ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር አድሪ አዙላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዘንድሮውን የድርጅቱ የሰላም ተሸላሚ መሆንን ይፋ አድርገዋል።

የላይቤሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እና የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎን የተካተቱበት የዩኔስኮ የተሸላሚዎች መራጭ ኮሚቴ ነው ምርጫውን ያከናወነው።

From: FBC

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s