ወጣቶችን መሳሪያ

የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ‹‹ወጣቶችን መሳሪያ ማስታጠቅና ማደራጀት›› የሚል ክስ ቀረበባቸው
.
.
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ታስረው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡
አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ታስረው የሚገኙ የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ጠይቀው ሲመለሱ መሆኑን የአብን ሊቀመንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አመራሮቻቸውና አባሎቻቸው የታሰሩት በቀዝቃዛ ቦታ፣ የፀሐይ ብርሃን በማያገኙበትና ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በማይችል ሁኔታ በመሆኑ እንዲሻሻልላቸው ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተው ሲወጡ፣ መውጫ በር ላይ አቶ ክርስቲያንን እንደያዟቸው ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡
በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው መርማሪ ፖሊስ በነጋታው ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ፣ ምድብ ወንጀል ችሎት እንዳቀረባቸውም አስረድተዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ለምን አቶ ክርስቲያንን በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸውና እንዳሰራቸው ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፣ ተጠርጣሪው ወጣቶችን መሣሪያ እንደሚያስታጥቁና እንደሚያደራጁ በማስረዳት ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት መጠየቁም ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪው አቶ ክርስቲያንም ወጣቶችን መመልመልና ማደራጀት ሥራቸው መሆኑንና ከእስርም ሲለቀቁ የሚቀጥሉት ሥራቸው እንደሆነ ተናግረው፣ መሣሪያ ያስታጥቃሉ ስለተባለው ግን ፖሊስ ማስረጃ ካለው እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ፣ ለሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ – ሪፖርተር ጋዜጣ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s